Discover
DW | Amharic - News

22 Episodes
Reverse
ናማታኒ ክዌክዌዛ በ18 ዓመቷ ነበር WELEAD TRUST የተባለ ወጣት መሪዎችን የሚያሰለጥንና በፖለቲካ ውሳኔዎች ሂደቶች እንዲሳተፉ የሚሠራ ድርጅት የመሠረተችው።በተባባሰው የዚምባብዌ ጨቋኝ ድባብ ክዌክዌዛ ለሕግ የበላይነትn ለፖለቲካዊ ተሳትፎ ትታገላለች፤ታስራለች፤ቁም ስቅልና የማስፈራሪት ሙከራዎች ደርሰውባታል። ስኬት ዋጋ ያስከፍላል ትላለች።
የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት የታሪክ መምህርና የማኀበራዊ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ተፈራ ኃይሉ፣የሰሞኑበክብረ በዓል፣እንደ ሻምበል ከተማ ጆባ ሁሉ በኮሪያ ዘመቻ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ምስጋና ለማቅረብ የተዘጋጀ እንደነበር ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
የኮንጎ ዴሞክራቲክ መንግስትና ኤም23 ባለፈው ሀምሌም ከሰላም ምምነት ደርሰው የነበር ቢሆንም ሁለቱም ስምምነቱን ሳያከብሩ ነበር የቆዩት። ያሁኑ ስምምነት በቀጣይ ሊሚደረጉ ድርድሮች መነሻ በመሆን እንድሚያገልግል የታመነ ሲሆን፤ ከበፊቱ ስምምነት የየለየ እንደሆነና ለተግብራዊነቱ የሚሰሩ---
በዓለም ዙሪያ በሚካሔዱ ግጭቶች ምግብ እንደ የጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ጸሀፊ ተናገሩ። በዓለም 673 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች እንደራባቸው ወደ መኝታቸው ይሔዳሉ። ከእነዚህ ውስጥ 307 ሚሊዮን አፍሪካውያን ናቸው። አሚና መሐመድ ዓለም ረሐብን ከማቆም ይልቅ ለወታደራዊ ወጪዎች ትኩረት እንደሰጠ ተችተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ማርበርግ የተሰኘው ተሐዋሲ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል። በዚህ ምክንያትም የሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ማርበርግ ተሐዋሲ የኤቦላ ተሐዋሲ ቤተሰብ ከሚባሉት አደገኛና ለሞት ከሚያደርሱ ተሐዋሲያን አንዱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለመሆኑ በቅርብ ዓመታት የዘር ማጥፋት ወይም የጦር ወንጀል የተፈፀመዉ ናይጄሪያ ይሆን? ብቻ ዶናልድ ትራምፕ 8 ጦርነት አስቁሜያለሁ ይላሉ፣ትራምፕ እንደ ጠቅላይ አዛዥ የሚያዘምቱት ጦር ሶማሊያን፣ የመንን፣ ኢራንን፣ የቬኑዙዌላ ጠረፍን ይደበድባል አሁን ደጎሞ ናጄሪያ ላይ እየዛቱ ነዉ
ቢያንስ 5 ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪቃ ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች ተገድለዋል። በደቡብ አፍሪቃ የተባበሩት የኢትዮጵያውን ማኅበረሰብ ማኅበርና አንድ የማኅበረሰብ አንቂ በጆሀንስበርግ እና አካባቢው እንዲሁም በደርባን ኢትዮጵያውያኑን የገደሉት ወንጀለኞች መሆናቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል፤ ሌሎች ግድያዎችም ደርሰው ሊሆን ይችላልም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጅንካ ከተማ «ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ነው» ያለው የሄሞራጂክ ፊቨር መከሰቱን ገልጿል። በበሽታው የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎችም እንዳሉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳሬክተር ለዶይቸ ቬለ እንዳስረዱት እስካሁን ተመሳሳይ ምልዕክቶች ያሳዩ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል።
የውጭ ምንዛሪ ግብይት በአቅርቦት እና ፍላጎት እንዲወሰን ከተደረገ ወዲህ ኢትዮጵያ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ ዕድገት ቢያሳይም ብር እየተዳከመ ነው። የወርቅ ኤክስፖርት መሻሻል ብር እንዲረጋጋ ሊያደርግ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ተስፋ አድርጓል። ሦስት ባለሙያዎች የተሳተፉበት ውይይት የምንዛሪ ገበያው ብር ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ይፈትሻል።
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ሊጠናቀቅ የቀረዉ ሦስት ወራት ገደማ ነዉ። ኮሚሽኑ ከህዝብ ያሰባሰባቸዉን ጥያቄዎችና አጀንዳዎች ለመንግሥት ያቀርባል።በሌላ በኩል በያዝነዉ 2018 ዓመት ብሔራዊ ምርጫ መካሄድ ይኖርበታል። ይሁንና መንግሥት ከህዝብ ለተሰበሰቡት አጀንዳዎች ከምርጫ መፊት መልስ ለመስጠት ጊዜና አቅም ይኖረዉ ይሆን?
ህወሐት በአለፈው እሁድ ባሰራጨው መግለጫ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትን የፕሪቶርያ ውል በመጣስ በትግራይ ግጭት ለመፍጠር በአፋር እና በምዕራብ ትግራይ ታጣቂዎች እየመለመለ እና እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል።
በኢትዮጵያ “ኤምፖክስ” ተብሎ በሚጠራው ተሀዋሲየተያዘ ሰው ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ አከባቢ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የአከባቢው የጤና ባለሙያ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት የበሽታው ምልክት የተወሰኑ ሰዎች ላይ ቢታይም በተዋህሲው መያዝ አለመያዛቸው ገና በምርመራ እስኪረጋገጥ ይጠበቃል፡፡
በኢኳቶሪያል ጊኒ ማርቡርግ በተባለ በጣም አደገኛ እና ተዛማች ተህዋሲ የተለከፉ ሰዎች መገኘታቸዉ ተገለፀ። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስታወቀዉ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች መካከል እስካሁን ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ሞተዋል። የኢኳቶሪያል ጊኒ መንግስት በሽታዉ በተዛመተባቸዉ አካባቢዎች ላይ «የጤና ማስጠንቀቂያ» አዋጅ ደንግጓል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሲኖዶሱ ቀኖና እና ዶግማ ውጪ መፈጸሙን ያወገዘችው በሦስት ሊቃነ ጳጳሳት የተመሠረተ የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ ጉዳይ ማወዛገቡን ቀጥሏል። ዶቼ ቬለ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን አነጋግሯል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተገደበ ነው። መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ በቅርቡ ዘርፉን የተቀላቀለው የኬንያው ሳፋሪኮም የሚያቀርቡት መደበኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አዲስ አበባን ጨምሮ እንደተገደበ ነው።
መንግሥት እስከ አሁን ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ለስድስት ገዢ ሀገራት ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ የ3 ሚሊዮን ኩንታል ውል መፈረሙን አስታውቋል። የረድኤትና ሌሎች የሀገር ውስጥ ድርጅቶችም ከውጭ የሚገዙትን ስንዴ በሀገር ውስጥ እንዲተኩ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል የውል ስምምነት በመፈረም ላይ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዱባይ ማራቶን ዳግም እጅግ አመርቂ ውጤት አስመዝግበዋል። በወንዶች 12ኛ ደረጃውን ብቻ ጣልቃ በማስገባት ከ1ኛ እስከ 13ኛ እንዲሁም በሴቶች ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃውን ተቆጣጥረውታል። በሆንግ ኮንግ የማራቶን ሩጫም ድሉ የኢትዮጵያውያን ሆኗል። የእግር ኳስና ሌሎች መረጃዎችም ተካተዋል።
እንደዚያም ሆኖ ግን አሁን ዓለም ስለ ቱርክ የሚያወራው ስለምርጫ አልያም ስለወቅታዊው ፖለቲካ እሰጥ አገባ አይደለም። አሁን ስለቅድመ ምርጫ የውጤት አንድምታ የሚወራበት ጊዜም አይደለም ። ቱርክ ታማለች። በደቡባዊ ቱርክ የምትገኘው የጋዚያንቴፕ ከተማ የርዕደ መሬቱ ያስከተለባት ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመቱ አሰቃቂ ነው።
ከሕዳር 2012 ጀምሮ የተካሔዱ ሶስት ሕዝበ-ውሳኔዎች የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልልን አራት ከፍለው ታሪክ ሊያደርጉት ነው። ክልሉን ወደ መፍረስ የገፉ ጥያቄዎች ምን ያክል ተመለሱ? ይኸ ውይይት የኢትዮጵያ መንግሥት የተከተለውን አካሔድ፣ ሕዝበ-ውሳኔዎቹን እና አዲሶቹ ክልሎች የነዋሪዎችን ህልም ለማሳካት የሚጠብቃቸውን ፈተና ይፈትሻል።
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ላለፉት አምስት የዝናብ ወቅት በዝናብ እጦት የተሰቃየው ማህበረሰብ አሁን ደግሞ ለህይወት ወደ ሚያሰጋው የድርቅ ተጽእኖ ምዕራፍ መሸጋገሩ ተገልጿል፡፡ በዞኑ ከሚገኙ 7.2 የአንስሳት ሃብት 2.3 እና ከዚያ በላይ የሚገመቱ ድርቁን ባለመቋቋም ማለቃቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡






















